(Khayyam) Rubaiyat XXVII
Myself when young did eagerly frequent Doctor and saint, and heard great Argument About it and about: but evermore Come out by the same Door as in I went. Bewketu Seyoum's translation በወጣኒነቴ በእድሜዬ አፍላ ጀንበር የሊቅ የጣዲቁን ሁለገብ ሀተታ አዘወትር ነበር እና ምን ተረፈኝ ? ተመልሼ ወጣሁ በገባሁበት በር፡፡ ሙሉና ጎደሎ የሞላ ማድጊያ ከጀርባ ካዘሉ ጎዶሎ ቅምጫና ያዘሉት ተሸሉ ሙሉ ያዘሉቱ ከላይ ያፈሳሉ ጀርባቸውን ከታች ያበሰብሳሉ ጎዶሎ ያዘሉ ምን ቢንገላጀጁ ምን ቢንገዋለሉ መሙላትን ይሻሉ ምሉዕ ነን የሚሉ እያደር ሲጎሉ ይንቦጨቦጫሉ፡፡ -ይስማዕከ ወርቁ ፀሎትና ዛቻ እድሌን ከግጥም ነፍሴን ከጥበብ አም የቋጠርካት አምላክ ያጣባሃት ጌታ ሌላም አለህ ስጠኝ ልሁነው በተር ስጠኝ ብዬ ብዬ ለምኜ ለምኜ የነፈከኝ እነደ ከለህበት ድረስ እራሴ መጥቼ ያለህን በመላ እወስድብሓለሁ፡፡ -ይስማዕከ ወርቁ ኩርኩም እልፍ ኩርኩሞችን የቀመሱ ራሶች ዳሳሽ እጆች እንጂ አይሹም ትራሶች፡፡ -ይስማዕከ ወርቁ ላባቴ ሰው ብቻ አይደለህም ካፈር ወጥተህ ላፈር መላዕክ ነህ ሉሲፈር ክብርህ ማንነትህ ባመፅ የሚታፈር የማትንበረከክ የማትርመጠመጥ ከባለጌ ዙፋን በርጩማ ምትመርጥ ያለ ባህር ሰርጓጅ … ያለ ሙሴ በትር በመታገስ ብቻ ባህር የምትመትር ካዘልኸኝ ጀምሮ እንኮኮ ጫንቃህ ላይ ከፍታውን እንጂ ዝቅታዉን ሳላይ እንደ ንስር መጠቅሁ እንደ ምስራቅ በራሁ የገዛ ክንፎቼን እንደ ዳንቴል ሰራሁ በርግጥ ደሃ ነበርክ ከሰላምታ በቀር የማታበረክት ነጠላህ መናኛ ሰውነትህ የክት በርግጥ ደሃ ነበርክ የነጣህ የጠራህ ከጦር ሜዳ ይልቅ ገቢያ የሚያስፈራህ ቤሳ ባታወርሰን አወረስከኝ ትግል የትም እንዳይጥለኝ ህይወት እንደ ፈንግል አባዬ ብርሃን አባ የምስራቅ በር ገመና ሸሻጊ እንደ ካባ ገበር አባቴ ባትሆን ይፀፅተኝ ነበር፡፡ -በዕውቀቱ ስዩም |
|
|
አሸባሪ
ሀገሬ እንጦሮንጦስ እያየሁ ስትገባ መቼም ሰው ነኝና ቢመጣብኝ እንባ እንዴት ብዬ ላልቅስ ፊቴ ተቀምጦ “አሸባሪ” ሚል ክስ፡፡ © MiliyoN ሳቅሽ ነው ገዳዬ
ጠላቶቼ ሁሉ በከንቱ ደከሙ ሊገድሉኝ ፈልገው ክላሽ ተሸከሙ ተራራውን ናዱ ገጀራ ሞረዱ ጦራቸውን ሳሉ እኔኑ ሊገሉ አቤት አለማወቅ አቤት የዕውቀት ማጠር ልፉ አላቸው እንጂ ሳቅሽን ቢያሳዩኝ እኔ ሞት አልነበር፡፡ © MiliyoN ፍፁምነት
ተብሎ ይጠራ እንጂ ፍፁም በሚባል ስም፥ ወደ ፍፁምነት የሰው ልጅ አይደርስም፡፡ © MiliyoN ለከት
ሀሳብህን ለመግለፅ አፍህን ስትከፍት አኑር ላፍህ ለከት በክፍት አፍህ በኩል ሰው ያንተን ጭንቅላት እንዳይመለከት፡፡ © MiliyoN ፌስ ቡክ
በእለተ ምፅዓት ፊቱ ላይ ይታያል የእያንዳንዱ ሐጥያት ፥ ያ ከሃሌ ኩሉ ታምሩ ማያልቀው ዙከርበርግን ልኮ ይሄንን ከብት ህዝብ የራሱን ኃጥያት በገዛ ገፁ ላይ እንዲፅፍ አረገው፡፡ © MiliyoN ረቡኒ
አስተማሪ አትበሉኝ ከክርስቶስ ጋራ እኩያ አድርጋችሁ እንዳታስቀስፉኝ! አስተማሪ አትበሉኝ እንዳታሰቅሉኝ የሰማዩን መምህር የሰቀሉ ሁሉ የመሬቱን እኔን እንዴት ይምራሉ? © MiliyoN ፍርድ
አዎ እቺ ዘማ... ሞት ነው የሚገባት ብላችሁ ካላችሁ በድንጋዩ ወግሮ ይግደላት ብያለሁ ፀዓዳ ሰው ካለ ከመሐከላችሁ! © MiliyoN ያኔ…
ውዴ … ወስፋታም ቀጫጫ ብለሽ አትናቂኝ አንቺ እንድትወፍሪ ወስፋታምሽ እኔ መክሳት ነበረብኝ አንተ አጭር ጉቶ ብለሽ አትበይኝ እንድትረዝሚልኝ ነው እኔ ያጠርኩትኝ ውዴ … ጠቋራ ነህ ብለሽ አትራቂኝ አንቺ እንድትቀይልኝ ፍሙን እፍ እያልኩኝ … መጥቆር ነበረብኝ ፉንጋ ነህ አትበይኝ አንቺ እንድታምሪ ነው ፉንጋ የሆንኩትኝ ውዴ…. አንተ ነህ ያወፈርከኝ ?፤ አንተ ነህ ያቀላኸኝ? አንተ ነህ ያረዘምከኝ ?፤ አንተ ነህ ያጎላኸኝ? አደራ … አደራ የኔ ውድ እንዲህ እንዳትይኝ ያኔ…. እሱ እኔን ትቶ እሱ እኔን ዘንግቶ አንቺ ላይ ሲጠበብ ሰዓቱን በሙሉ ገጽሽ ላይ አጥፍቶ እሱ እኔን ትቶ አንቺን ሲያቀላ አንቺን ሲያሳምር አንቺን ሲያረዝም አንቺን ሲያወፍር ጌታ የ’ኔን ሰዓት ያኔ … ላንቺ ባይገፈትር መቼ ፉንጋ ፣ጉቶ አጭር እባል ነበር?! © MiliyoN 8ኛዋ አህጉር
አህጉር ከመሆኗ በፊት ፹ ሀገራትን አቃፊ ሐገር ነበረች አሉ ኢትዮጵያ እጅጉን ሰፊ አንድ አርጎ መግዛት ያቃተው ፈርኦን መጣና ዛሬ አህጉር ሆነች ሀገሬ! © MiliyoN ጆሮ ለነጃችን
ሁሉን ቻይ የሆንከው ባክህ ለገዣችን ሰሚ ጆሮ ስጠው የለም ታሁን ወድያ ጆሮ አልሰራም ካልከኝ ይኸው የተሰራ ግድ የለም ጌታዬ የማልሰማ ልባል ልውጣ ከሰው ተራ ብቻ የገዣችን የዛ የነጃችን የሱ ጆሮ ይስራ:: © MiliyoN አለሁ
እውን እኔ አለሁ? ብዬ ጠይቃለሁ ይህን በማለቴ በሕይወት መኖሬን አረጋግጣለሁ፡፡ -Albo ሰላም ሰላሜን የነሳህ አንተ ሁነህ ሳለህ ሰላም ያስፈልጋል ለምን ትለኛለህ፡፡ -Albo ቻው ላልመለስ ዳግም ስሄድ ተለይቼሽ ጠግቤሽ ነበረ እልፍ ጊዜ አይቼሽ፡፡ ስጦታህን ውሰድ እግርህ ስር ወድቄ ተንሰቅስቄ አልቅሼ… አልቅሼ….. እንባዬን አፍስሼ የእንባዬን ዋጋ ሽልማት ብትስጠኝ በገዛ ጥረቴ የመጣ መሰለኝ፡፡ ሁሉን ረስቼ ሽልማቱ ካንተ መምጣቱን ዘንግቼ በከንቱ ውዳሴ ኩራተኛ ብሰኝ ሽልማቴን ወስደህ ውርደቴን አልብሰኝ፡፡ -Albo ቁጥር ጨረቃን ለመንካት የሰው ልጅ ወደ ላይ ወደ ህዋ ሲበር ቁጥር ባይኖር ኑሮ ምን ይውጠው ነበር? -Albo መባ አንተ ሁነኝ እንጂ እኔስ በምን አቅሜ ግደለኝ ያልኩህ ነኝ አንደ ቀን ታምሜ ትንሽዬ እንቅፋት ጥፍሬን ብትነርተዉ ገላዬ መታገስ መቋቋም አቃተዉ በዚች አስቃያሚ ዉዥንብር መጥፎ አለም ይሄ ነዉ ትክክል ያኛዉ ነዉ አልልም በዚህች ደንባራ ዉስጥ ፈጥረኸኝ ሳለ ቅንጣዓት ጥበብህን ብትሰጠኝ ምናለ ከጣቃ አዉጥተህ ያሳየኽኝ ማሕቶት እባክህ ተቀበል የኔን የምስኪኑን የድሃዉን ጸሎት፡፡ |